letras.top
a b c d e f g h i j k l m n o p q r s t u v w x y z 0 1 2 3 4 5 6 7 8 9 #

letra de atenekuat - bisrat surafel (ብስራት ሱራፌል), lij michael

Loading...

yeah ብስሬ
ካሙዝ
ልጅ ማይክ
yeah
እንሂድ

ያች እርግብ የዋህ ነች አንጀት የምትበላ
ትርፍ ክንፍ የላትም አትንኳት በባላ
ያች እርግብ የዋህ ነች አንጀት የምትበላ

ፀባይዋ ፍቅር ነው አመሏ ዝምታ
ያኔ እኔን አያርገኝ ሰው የነካት ለታ

ትመላለስ ባይኖቼ ትብረር በልቤ ሰማይ
ውዬ ማደር አልችልም ሰላም መሆኗን ሳላይ
ላላምዳት እንጅ አቅርቤ ትረፍ በልቤ ገብታ
መቸም ጠላፊ አያልፋት ተዉባ እንዲህ ቆንጅታ (ቆንጅታ)

ለኔ እሷ ገዴ (ገዴ)
የእድሌ መገኛ (መገኛ)
የነኩብኝ እንደው (እንደው)
ከልካይ የለ ዳኛ (ዳኛ)
ለኔ እሷ ገዴ (ገዴ)
የእድሌ መገኛ (መገኛ)
የነኩብኝ እንደው (እንደው)
ከልካይ የለ ዳኛ (ዳኛ)
ጥበብን ተውሳ ከናትና አባቷ
እዩኝ እዩኝ ሳትል ደምቃለች ልጅቷ
ግርማ ከሞገሱ እሱም አድሏት
ስንቱ ለጠለፋ ተማከረባት
እያዩ ነው ማለፍ አለኝ ብሎ ብስራት
ነገር እንዳይመጣ ባላ ተሰዶባት
ይቀስሙታል እንጅ ቆንጆን እንደ አበባ
እንዴት ይሰደዳል ወንጭፍና ባላ
ይኸን ይኸንን ሳይ ቀረው ከመንገዴ
ብለው የዘፈኑት ለዚህ ይሆን እንዴ
እኔም ቀርቻለሁ ከመንገዱ እንዳልኩሽ
የወዳጄ ወዳጅ ሁነሽ በመምጣትሽ

ያች እርግብ የዋህ ነች አንጀት የምትበላ
ትርፍ ክንፍ የላትም አትንኳት በባላ
አመሏ ፍቅር ነው ፀባይዋ ዝምታ
ያኔ እኔን አያርገኝ ሰው የነካት ለታ

ስናገር እስለዋለው ደግሜ ደጋግሜ
ለንስፍስፍ የዋህ ልቧ አለሁለት ዘብ ቆሜ
ሰው አለሽ እኔን መሳይ በመውደድሽ ሚኩራራ
ስጠብቅሽ በእምነቴ እንቺ ፍቅሬን አደራ (አደራ)
ለኔ እሷ ገዴ (ገዴ)
የእድሌ መገኛ (መገኛ)
የነኩብኝ እንደው (እንደው)
ከልካይ የለ ዳኛ (ዳኛ)
ለኔ እሷ ገዴ (ገዴ)
የእድሌ መገኛ (መገኛ)
የነኩብኝ እንደው (እንደው)
ከልካይ የለ ዳኛ (ዳኛ)

letras aleatórias

MAIS ACESSADOS

Loading...