letra de aykedashem lebe - tilahun gessesse
Loading...
የትዝታዬ እናት የስሜቴ እመቤት
የፍላጎቴ ምንጭ የእድሌ ባለቤት
የምታስታውሺኝ ያለፍኩትን ደስታ
አንቺ ብቻኮ ነሽ የኔ ልብ አለኝታ
ያሳለፍነው ዘመን ደስታን ያየንበት
ተመልሶ ቢገኝ አሁን ምናለበት
ያሳለፍነው ዘመን ደስታን ያየንበት
ተመልሶ ቢገኝ አሁን ምናለበት
እህ እህ…እህ እህ
እህ እህ እህ
አሄ…አህ አህ
የተጫወትነዉን ምንግዜም አልረሳም
እንዲህ ተለያይተን በናፍቅት ብከሳም
አይከዳሽም ልቤ ሰው መክዳት አያውቅም
እስኪለያይ ድረስ ከለቅሶ ከሳቅም
ያሳለፍነው ዘመን ደስታን ያየንበት
ተመልሶ ቢገኝ አሁን ምናለበት
ያሳለፍነው ዘመን ደስታን ያየንበት
ተመልሶ ቢገኝ አሁን ምናለበት
እህ እህ…እህ እህ
እህ እህ እህ
አሄ…አህ አህ
ዉበትሽን እንዳላይ እርቄም ማርኮታል
ልቤ ግን ግልፅ ነው ተይ ስሚኝ
መዝግቦ ይዞታል
ባካል ባላይሽም ወይ ባሳብ ግስጋሴ
አልተነጣጠልንም አዎ ነፍስሽ እና ነፍሴ
ያሳለፍነው ዘመን ደስታን ያየንበት
ተመልሶ ቢገኝ አሁን ምናለበት
ያሳለፍነው ዘመን ደስታን ያየንበት
ተመልሶ ቢገኝ አሁን ምናለበት
እህ እህ…እህ እህ
እህ እህ እህ
አሄ…አህ አህ
letras aleatórias
- letra de happiness - 青山テルマ (thelma aoyama)
- letra de ybludok - eiia
- letra de suniye to (romanized) - abhijeet
- letra de exuvia - zanias
- letra de runaway - keagan grimm
- letra de the way to do it - мс сенечка (mc senechka)
- letra de head work - big yba
- letra de dat's right - adawnis eternal
- letra de run away - chezile
- letra de дурень (fool) - бумбокс (bumboks)