letra de ethiopia - neway debebe
አሄሄ…
ሲሳዬ ሲሳዬ
እድሌ ቤዛዬ
ጀማዬ ጀማዬ
ዝናር ገበያዬ
ዞሮ መግቢያዬ
አሄሄ…
ሲሳዬ ሲሳዬ
እድሌ ቤዛዬ
ጀማዬ ጀማዬ
ዝናር ገበያዬ
ዞሮ መግቢያዬ
ኢትዮጵያ(3×) ሀገራችን
ኢትዮጵያ እናታችን
እንዳመላችን ሰብሳቢያችን ዜግነታችን መጠርያችን
በሴቲት ሁመራ በገዳሪፍ ካርቱም(3×)
ጅቡቲ ኬንያ ያንግዜ ሳዘግም (በእግሬ ሳዘግም) ብቻዬን ሳዘግም
በርሀ ሳቋርጥ በስደት ዘመቻ
የተከተለችኝ ባንዲራዬ ብቻ
ፀንታ ያፅናናችኝ
ኮርታ ያኩራራችኝ
ትዕግስት ያደለችኝ
ያበረታታችኝ
የደፈረው ጫካ የፈራው ሰው ሀገር (3×)
እግሬ አውጪኝ እያለ ድንበር ኬላ ሲሰብር (3×)
ዛሬ በሰው ሀገር ኑሮውም ቢከፋ
ሀይማኖቱን ይዞ ይኖራል በተስፋ
ጠንክሮ እየሰራ ለፍቶ እየተማረ
ሁሉ ያልፋል በማለት እድሜ እየቆጠረ
ያስለቅሳል ያስተክዛል
ያሳለፍነው መች ይረሳል
ያስለቅሳል ያስተክዛል
የእኛስ ነገር መች ይረሳል
ሮም ላይ ያላችሁ (እንደምን ናቹ)
ለንደን ያላችሁ (እንደምን ናቹ)
ጀርመን ያላችሁ (እንደምን ናቹ)
ፓሪስ ያላችሁ (እንደምን ናቹ)
ሆላንድ ያላችሁ (እንደምን ናቹ)
ስዊድን ያላችሁ (እንደምን ናቹ)
ሰላምታዬ ይድረሳችሁ
አሄሄ…
ሲሳዬ ሲሳዬ
እድሌ ቤዛዬ
ጀማዬ ጀማዬ
ዝናር ገበያዬ
ዞሮ መግቢያዬ
ኢትዮጵያ(3×) ሀገራችን
ኢትዮጵያ እናታችን
እንዳመላችን ሰብሳቢያችን ዜግነታችን መጠርያችን
በማናውቀው በሐል ባልጠቀመን ነገር 3×
ሶሻሊስት ኮሚኒስት ቀይ ሽብር ነጭ ሽብር
እያልን ቀይ ሽብር ቀይ ሽብር ነጭ ሽብር
ስንት ሰው መነነ ተሰደደ ከሀገር
ስንቱ እስር ቤት ገባ ስንቱስ በላው አፈር
ከወዳጅ ዘመዱ እየተነጠለ
ስንቱስ ተባረረ ስንቱስ ተገደለ
ካለፈው ተምረን ካደረግነው ጥፋት 3×
እስቲ እንተባበር ኢትዮጵያን ለማንሳት
ህዝቧን ባንዲራዋን ታሪኳን አስታውሱ
ታጋሽ ይቅር ባይዋን ኢትዮጵያን አትርሱ
ሁሉን ሰብሳቢዋን
የወላድ ደሀዋን
በፀሎት ኗሪዋን
ፍቅር መጋቢዋን
ያስለቅሳል ያስተክዛል
ያሳለፍነው መች ይረሳል
ያስለቅሳል ያስተክዛል
የእኛስ ነገር መች ይረሳል
አሜሪካ ያላችሁ (እንደምን ናቹ)
ካናዳ ያላችሁ (እንደምን ናቹ)
እስራኤል ያላችሁ (እንደምን ናቹ)
አቴንስ ያላችሁ (እንደምን ናቹ)
ኬኒያ ያላችሁ (እንደምን ናቹ)
ካርቱም ያላችሁ (እንደምን ናቹ)
ሳውዲ ያላችሁ (እንደምን ናቹ)
ሜልቦርን ያላችሁ (እንደምን ናቹ)
የመን ያላችሁ (እንደምን ናቹ)
ጅኔቫ ያላችሁ (እንደምን ናቹ)
(እንደምን ናቹ) 4×
letras aleatórias
- letra de skulls - sematary
- letra de fluorescencia - elias lugon
- letra de karma - tujay
- letra de hamants convo pt2 - govana
- letra de im the 1! - summrs
- letra de postcard - lil guac
- letra de puking on a pretty girl - the toilet bowl cleaners
- letra de the always coming aftermoment - trestin eeling
- letra de that's my - donell lewis
- letra de dokter - bots