letras.top
a b c d e f g h i j k l m n o p q r s t u v w x y z 0 1 2 3 4 5 6 7 8 9 #

letra de zew zew - jano band

Loading...

ከልጅ ከአዋቂው መስሎ ጓደኛ
ቀኑን ሳያርፈው ለሊት ሳይተኛ
ካዘነው ሲያዝን ከሳቀው ሲስቅ
እዚ እያጣላ እዛ ስያስታርቅ
ደሞ በሌላ ልቡ እስኪረታ
እችን ስያገባ ያችን ሲፈታ
ወጣ ገባ ሲል እዚም እዝያም
ቀደመው ጊዜ አንዱን ሳይዘው
እንዲያው ዘው ዘው
አዬ ዘው ዘው
ጥርስ የታደለው
አዬ ዘው ዘው
ስንቱን አሞኘው
አዬ ዘው ዘው
ስንቱን አቄለው
አዬ ዘው ዘው
ዛሬ አለፈና
አዬ ዘው ዘው
ጥርሶቹም አልቀው
አዬ ዘው ዘው
ሳይወርሰው ሽበት
አዬ ዘው ዘው
በድዱ ሳቀው
አዬ ዘው ዘው

ቀብሮ በውስጡ ከያዘው እውነት
በልጦ በስሙ ሲምል ሲገዘት
አፈ ቅቤው ሰው አለም ሳትበቃው
ሰማይ ልርገጥ ሲል መሬት እርቃው
በጠላው እውነት ዛሬ ተወርሶ
የኋላውን ሲያይ የፈራው ደርሶ
ጊዜ በቁጭት ሲወዘውዘው
ምኑን ይልቀቀው የቱን ይያዘው
እንድያው ዘው ዘው
አዬ ዘው ዘው
ጥርስ የታደለው
አዬ ዘው ዘው
ስንቱን አሞኘው
አዬ ዘው ዘው
ስንቱን አቄለው
አዬ ዘው ዘው
ዛሬ አለፈና
አዬ ዘው ዘው
ጥርሶቹም አልቀው
አዬ ዘው ዘው
ሳይወርሰው ሽበት
አዬ ዘው ዘው
በድዱ ሳቀው
አዬ ዘው ዘው

የሸሸለት ወዳጅ ጥርስ ላይመልሰው
አትሳቅ ለይምሰል ባክህ አንተ ሰው
ሰምቶ ከመናገር በቡና ቤት ወሬ
ትደርሳለህ ተመለስ ተው ስማኝ አጅሬ

አርገው ቸብ ቸብ ጊዜን ላይዙት
ወገብ ትከሻን ቢወዘውዙት
ወናውን ከርሞ እድሜ ካለለት
እንኳን ጭፈራው ወጡስ መች ሊጥም

አርገው ቸብ ቸብ ጊዜን ላይዙት
ወገብ ትከሻን ቢወዘውዙት
ወናውን ቀድሞ እድሜ ካለለት
እንኳን ጭፈራው ወጡስ መች ሊጥም

እንድያው ዘው ዘው
አዬ ዘው ዘው
ጥርስ የታደለው
አዬ ዘው ዘው
ስንቱን አሞኘው
አዬ ዘው ዘው
ስንቱን አቄለው
አዬ ዘው ዘው
ዛሬ አለፈና
አዬ ዘው ዘው
ጥርሶቹም አልቀው
አዬ ዘው ዘው
ሳይወርሰው ሽበት
አዬ ዘው ዘው
በድዱ ሳቀው
አዬ ዘው ዘው
አዬ ዘው ዘው
እሀ
አዬ ዘው ዘው

አዬ ዘው ዘው
እሀ
አዬ ዘው ዘው

letras aleatórias

MAIS ACESSADOS

Loading...