letras.top
a b c d e f g h i j k l m n o p q r s t u v w x y z 0 1 2 3 4 5 6 7 8 9 #

letra de 1995 (intro) - ap est

Loading...

[chorus]

1995 መጣው ወደዚች አለም
ተቀላቀልኩ ይህን ኑሮ ተሞላው በሰቀቀን
ተደስተን ሳንጨርስ ሀዘን ከሚቦርቅብን
አለም ከምትባል ቦታ ሚስጥሯም ከሚከብደን

ስቃዩም አበቃ ስል ችግሬም ቀለለ
ዞሮ ከብዶ መጣ ነገሩም ተቆለለ
ችግሬም በዛ ስል ቅንጣት ደስታ ይመጣል
ገና ሳላጣጥመው ተመልሶ ይሄዳል

[verse]

ደግሞ ይሉታል ልደት ደሞም ያከብሩታል
ስቃይ ያገኙበትን ቀን ይደሰቱበታል
ሰዉ ተሸውዷል ግራውም ገብቶታል
መከራ እና አበሳ እንዴት ደስታ ይሆናል

እንኳን ተወለድክ አሉኝስጦታንም ሰጡኝ
አብረን ስንስቅ ውለንበነጋታው አረሱኝ
ለልደቴ የወደዱኝ ዛሬ ላይ ለምን ጠሉኝ
ነገ ልደት ሲመጣ ተመልሰው ሊወዱኝ

አንድ ምርጫ ቢኖረኝ እል ነበር አትውለዱኝ
ቢያመልጥ ቢያመልጥ ሚያመልጠኝ ገንፎ ነው ሚቀርብኝ
ተዉ ተዉ አትውለዱኝ ተዉ ተው ይቅርብኝ
ከማገኘው ደስታ ይበልጥ ስቃይ ነው ሚበዛብኝ
አትበሉኝ እንኳን ተወለድክ
ከስቃይ ከችግር እየታገልኩ
አትበሉኝ መልካም ልደት
አትበሉኝ በልደት እንደሰት

chorus]

1995 መጣው ወደዚች አለም
ተቀላቀልኩ ይህን ኑሮ ተሞላው በሰቀቀን
ተደስተን ሳንጨርስ ሀዘን ከሚቦርቅብን
አለም ከምትባል ቦታ ሚስጥሯም ከሚከብደን

ስቃዩም አበቃ ስል ችግሬም ቀለለ
ዞሮ ከብዶ መጣ ነገሩም ተቆለለ
ችግሬም በዛ ስል ቅንጣት ደስታ ይመጣል
ገና ሳላጣጥመው ተመልሶ ይሄዳል

letras aleatórias

MAIS ACESSADOS

Loading...