letras.top
a b c d e f g h i j k l m n o p q r s t u v w x y z 0 1 2 3 4 5 6 7 8 9 #

letra de esregna - teddy yo

Loading...

አንቺ ሆነሽ ከሳሽም ጠበቃ
ለማን አቤት ልበል ሆነሽ ዳኛ
አንቺ ሆነሽ ከሳሽም ጠበቃ

ለማን አቤት ልበል ሆነሽ ዳኛ

ወንጀለኛ በፍቅርሽ ሆንኩኝ እስረኛ
ጉዳተኛ ያንቺ ቁስል አያስተኛ
ዝምተኛ አርጋኝ ነበር ብሶተኛ
ቅናተኛ እኔ ባንቺ ምቀኛ
አሳይኛ ጨለማውን አብሪልኛ
መገናኛ ነይ በመስኮቱ ጥሪኛ
አስፈጂኛ እዉነቱ ይውጣ ታረቂኛ
ይፍረድ ዳኛ እኮ ማነው ጥፋተኛ
አዳምጡኛ ጆሮ ስጡኝ ስሙኛ
ልቀቁኛ ልውጣ ላሳይ ባገርኛ
ተጓዥ ነኝ ተስፈኛ

አንቺ ሆነሽ ከሳሽም ጠበቃ
ለማን አቤት ልበል ሆነሽ ዳኛ
አንቺ ሆነሽ ከሳሽም ጠበቃ
ለማን አቤት ልበል ሆነሽ ዳኛ
አንቺ ሆነሽ ከሳሽም ጠበቃ
ለማን አቤት ልበል ሆነሽ ዳኛ
አንቺ ሆነሽ ከሳሽም ጠበቃ
ለማን አቤት ልበል ሆነሽ ዳኛ

ሹክሹክታ አምጪ እንጂ ጨዋታ
በጋጋታ ሳይፈጠር ሁካታ
አካፍሉታ የኔን ስንቅ ፋንታ
መልእክቷ ሲመጣልኝ በፖስታ
በዝግታ ይዞኝ ሄደ በትዝታ
መሪጌታ ሲያስተምሩ የኔታ
ቀሰምኩታ አዳምጬ በዝምታ
በችሎታ በፊደሎች ላፍታታ
እስቲ ቦታ ማይኩን ስጡ ለአፍታ
ልቀቁታ አትቅር ጥበብ ተገትታ
ቦታ እንስጠው ለይቅርታ

አንቺ ሆነሽ ከሳሽም ጠበቃ
ለማን አቤት ልበል ሆነሽ ዳኛ
አንቺ ሆነሽ ከሳሽም ጠበቃ
ለማን አቤት ልበል ሆነሽ ዳኛ

እኔ ምለው ማነው ጥፋተኛው
ወንጀል ሆኖ ማፍቀር
እኔ ነኝ ምርኮኛው
እኔ ምለው ማነው ጥፋተኛው
ተበዳይም ሆኜ እኔ ነኝ እስረኛው
እኔ ምለው ማነው ጥፋተኛው
ወንጀል ሆኖ ማፍቀር
እኔ ነኝ ምርኮኛው
እኔ ምለው ማነው ጥፋተኛው
ተበዳይም ሆኜ እኔ ነኝ እስረኛው

አንቺ ሆነሽ ከሳሽም ጠበቃ
ለማን አቤት ልበል ሆነሽ ዳኛ
አንቺ ሆነሽ ከሳሽም ጠበቃ
ለማን አቤት ልበል ሆነሽ ዳኛ
አንቺ ሆነሽ ከሳሽም ጠበቃ
ለማን አቤት ልበል ሆነሽ ዳኛ
አንቺ ሆነሽ ከሳሽም ጠበቃ
ለማን አቤት ልበል ሆነሽ ዳኛ
ለማን አቤት ልበል ሆነሽ ዳኛ
ለማን አቤት ልበል ሆነሽ ዳኛ

ለማን አቤት ልበል ሆነሽ ዳኛ

letras aleatórias

MAIS ACESSADOS

Loading...