letras.top
a b c d e f g h i j k l m n o p q r s t u v w x y z 0 1 2 3 4 5 6 7 8 9 #

letra de agezegh - hana tekle

Loading...

ለውድቀት ፡ መሮጤ ፡ ምንድነው
ማዳንህ ፡ የገባኝ ፡ ጥንት ፡ ነው
አባቴ ፡ ልጄ ፡ አንቺ ፡ የኔ ፡ እያልከኝ

የጎረቤት ፡ ኑሮዬ ፡ ናፈቀኝ
ጥፋቱ ፡ ከጠላት ፡ ወይ ፡ ከኔ
ገብቶኝ ፡ እንዳልገባው ፡ መሆኔ
አመል ፡ ካልሆነብኝ ፡ በስተቀር
አሁን ፡ ምን ፡ ይገኛል ፡ ጠላት ፡ ሰፈር

አዝ: – አግዘኝ ፡ ደግፈኝ
ብቻዬን ፡ አቅም ፡ የለኝ
ያየህልኝን ፡ ቁም ፡ ነገር
እንዳላጣው ፡ በተራ ፡ ነገር (፪x)

ማን ፡ አየኝ ፡ አላየኝ ፡ ኑሮዬን
አልደብቀው ፡ ካንተ ፡ ገበናዬን
ሰው ፡ ፈርቶ ፡ ሰው ፡ ሸሽቶስ ፡ እስከመቼ
ልኑር ፡ መጀመሪያ ፡ አንተን ፡ ፈርቼ
እንዳልሞት ፡ ነበረ ፡ መዳኔ
ፈቅደህ ፡ የሞትክልኝ ፡ ካህኔ
እያወቅኩ ፡ ከገባሁ ፡ ከእሳቱ
ማን ፡ ሊመልሰኝ ፡ ነው ፡ ማን ፡ ብርቱ

አዝ: – አግዘኝ ፡ ደግፈኝ
ብቻዬን ፡ አቅም ፡ የለኝ
ያየህልኝን ፡ ቁም ፡ ነገር
እንዳላጣው ፡ በተራ ፡ ነገር (፪x)

ነጻነቴም ፡ በዛ ፡ መሰለኝ
ምን ፡ አለበት ፡ ኑሮ ፡ ለመደኝ
ቀለለኝ ፡ የጥፋት ፡ መንገዴ
ላይቀርልኝ ፡ ካለፈ ፡ መንደዴ
የማውቀውን ፡ እውነት ፡ ሳልገፋ
ከበር ፡ መልስ ፡ ሳልሆን ፡ ሳልጠፋ
ብላቴናነቴን ፡ ታደገው
አውለው ፡ ከቤትህ ፡ ከሚበጀው

አዝ: – አግዘኝ ፡ ደግፈኝ (ደግፈኝ)
ብቻዬን ፡ አቅም ፡ የለኝ (ብቻዬን—-አቅም ፡ የለኝ)
ያየህልኝን ፡ ቁም ፡ ነገር (ያየህልኝን—-ቁም ፡ ነገር)
እንዳላጣው ፡ በተራ ፡ ነገር (እንዳላጣው—-ተራ ፡ ነገር) (፪x)

letras aleatórias

MAIS ACESSADOS

Loading...